ዜና - ቅዳሜን ለስፖርት ፤ በ21.09.2019 ቀን ስፖርት ለልጆች እና ለወጣቶች!!


     በሙያዬ  የስፖርት አሰልጣኝ ነኘ ፣ በአካባቢያቸን  በሚገኙ የስፖርት ክለቦችና ነዋሪዎች እንዲሁም በስደተኞች መካከል ማህበርዊና ሰፖርታዊ ትስስር መፍጠር አንዱ ስራዬ ነው ፡፡
እርስዎ በሃገርዎ እያሉ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር ወይ? አሁንስ እዚህ ባሉበት አካባቢ የስልጠና እድል ቢያጋጥመዎ ለመሰለጠን ፍልጎቱ አለዎት ወይ?  ከዚህ በፊት በምንም አይነት ሰፖርታዊ እንቅስቃሴ ተሳትፈው የማያዉቁ ከሆነ እንደ አዲስ ጀምረው ለመሰልጠን ፍልጎት አለዎት ወይ?
ይህ ከሆነ በዚህ ድህረ ገጽ በመጠቀም በጊንስሃይም ጉስታቨስቡርግ ውስጥ የሚገኘውን የስፖርት ክለቦችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ጀርመን ውስጥ በልዩ ልዩ የስፖርት ክለቦች ውስጥ መሳተፍ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ለመፍጠርና ያግዛል፡፡ ይህ ብእንዲህ እዳለ በየእለቱ የሚድርጉ  ስፖርታዊ ግንኝነቶች ጤንነትን ለመጠበቅና የጀርመንኛ ቋንቋዎን ለማሳደግ እጅግ ጠቃሚዎች ናቸው፡፡  በመሆኑም አባላቱ  ለማህበሩ የሚደር,ጉት የአባልነት መዋጮ በጣም ዝቅተኛና አቅምን ያገናዘበ ሲሆን ፣ የዚህ ማህበር ወይም ክለብ አባል በመሆን ይህን መልካም አጋጣሚ እና እድል እንዲጠቀሙበት እንጋባዛለን፡፡
ከዚህ በፊት በየትኛዉም ሰፖርት ዓይነት የማይሳተፉ ከሆነና ነገር ግን በክለቡ የመሳተፍ ፍልጎቱ ካለዎትና ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለዎት ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ ሊያገኙኝ ይችላሉ፣
ኢሜል: Diese E-Mail-Adresse ist vor Spambots geschützt! Zur Anzeige muss JavaScript eingeschaltet sein!
ሞባይል/ ዋትስአፕ ፣0170/5257627

ስፖርት ጊንስሃይም
 
የስፖርት ዓይነቶች  

እግርኳስ፣ቅርጫት ኳስ፣የጠረጴዛ ቴኒስ፣ እጅ ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ፣ ክብደት መነሳት፣አትሌቲክስ ፣ካራቴ ፣ጁዶ ፣ኪክ ፣ ቦክሲንግ ፣ ቼዝ፣  ዳንስ ፣ ጂምናስቲክስ /ጂምናስቲክስ የጤና ስፖርት እምብርት/ እና   ቦዉሌ፣ ካኑ፣ ሽታንድ አፕ ፓደሊንግ /ሽቴህፓድልን፣ ሴገልን፣ራድባል፣ ራድፖሎ፣ ሮልሹ ፣ኩንስትላውፍን፣ ቱርነን፣ ኪከቦክስን   

SKG Ginsheim

SKB Gustavsburg